=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
በዛሬው ትምህርታችን ከኢባዳ ተግባሮች አንዱ የሆነውን ስለ ዱአ እናያለን። በዚህ ትምህርታችን ከምንዳሳቸው ነጥቦች ውስጥ የዱአ ምንነት ፣ የዱአ አይነቶች ፣ የዱአ ታላቅነትና ጥቅሞች ፣ የዱአ ቅድመ ሁኔታዎች ፣ የዱአ ስነምግባር ፣ ዱአ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችልባቸው አጋጣሚዎችና ሁኔታዎች ናቸው።
ዱአ አሏህን ለዚህም ሆነ ለመጭው አለም እርዳታ የምንጠይቅበት ታላቅ መንፈሳዊ ኢባዳ ነው። በቋንቋ ደረጃ ዱአ ማለት የእርዳታ ጥሪ ማድረግ ወይም መለመን ፣ መጠየቅ ፣ እርዳታን መሻት ማለት ሲሆን በሸሪአ ፍች መሠረት ደግሞ ዱአ ማለት አሏህ(ሱ.ወ.ተ) የሆነ ነገር እንዲሰጠን እና ከመቅሰፍት ፣ ከመከራከና ከችግር እንዲጠብቀን መለመን ነው።
አሏህ በቁርአኑ በሱረቱ ጋፊር አንቀፅ 60 ላይ እንዲህ ይላል:-
=<({አል-ቁርአን 40:60})>=
{60} ጌታችሁም አለ! ለምኑኝ ምላሽ እሰጣችኋለሁና። እነዚያ እኔን ለመገዛት እብሪተኛ የሆኑ የተዋረዱ ሆነው ወደ ጀሃነም እሳት ይገባሉ።ዱአ የአንድን ሰው የኢማን ደረጃና ከሱ ጋር ተያያዥ የሆነውን የተውሂድ ማለት በተውሂድ ላይ ያለውን ዝንባሌና ጥንካሬ የሚያመላክት ነው።
ዱአ በጣም የተወደደ እና ትልቅ የአምልኮት ተግባር ሲሆን የሰው ልጅ ጌታውን በቀጥታ የሚያገኝበት መንገድ ነው። ከጌታውም ጋር ያለውን ትስስር የሚጠቁም ነው። ለዚህም ነው የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) "ዱአ በራሱ ኢባዳ ነው" ያሉት። እንዲሁም ዱአ የኢማን መገለጫ ነው። ምክኒያቱም ዱአ የሚያደርግ ሰው ለዱአው ምላሽ የሚሰጥ አንድና ብቻኛ አምላክ መኖሩን ስለሚያምን ነው። ድአ ትልቅ ኢባዳ ወይም የአምልኮት ተግባር ነው ከሚያስብለው ነገር አንዱ ከአሏህ ውጭ ላለ ነገር የሚደረግ ከሆነ አሏህ ፈፅሞ የማይምረው የሽርክ ተግባር የሚሆን በመሆኑ ነው።
ከአሏህ ውጭ ያለን ነገር መለመን ሰውም ይሁን እንስሳ ፣ ጣኦትም ይሁን መልእክተኛ ወ.ዘ.ተ መለመን ትልቅ ሽርክ ነው። በሌላ አነጋገር ሊለመን የሚገባው አንድ አሏህ ብቻ ነው። ማንም ቃልቻ ፣ ቆሌ ፣ ዛር ፣ ጠንቋይ ለማንም ሰው ችግር ወይም ተማፅኖ ወይም ዱአ ቅንጣት ታህል ምላሽ መስጠት አይችሉም! እደግመዋለሁ ቅንጣት ታህል ምላሽ መስጠት አይችሉም!!!
ስለዚህ ቢቸግረን ፣ ቢከፋን ወደ አሏህ ተመልሰን በቀጥታ እራሱ አሏህን መለመን እንጅ እገሌ ድረሱልኝ፤ አሊ ቆሌ ጠብቁኝ ፣ እገሌ ህይወቴን የተቃና እድርጉልኝ ብልን የውሸት አማልክቶችን መለመን የለብንም፤ ከእኛ ከሙስሊሞችም ፈፅሞ አይጠበቅም። ምክኒያቱም ክህደት ነው፤ የበደሎች በደል የሆነው ትልቅ ሽርክ ነው። ምንም እንኳ ለዱአችን ምላሽ ቶሎ ባናገኝ በሶብር ላይ ሁነን ደግግመን አሏህን መለመን ይኖርብናል እንጅ የውሸት አማልክቶችን አማራጭ አድርገን መያዝ የለብንም። ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) "የሰማይን በር ያንኳኳ ሳይከፈትለት አይቀርም" ብለዋል። አዎ በመተናነስ ፣ ለሊት ላይ በመቆም ያ– አላህ ያ— ወዱድ ያ— ሙጂብ ብለን በሚወዳቸው 99 ስሞቹ እየተጣራን አልቅሰን በሮቹን ስናንኳኳ አላህ የረህመት በሩን ይከፈፍትልናል።
አንድ ገጠሬ ወደ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) መጣና ያ ረሱለሏህ! ብሎ ጠራቸዉና ረበና(ጌታችን) ቅርብ ነው እንመሳጠረዉ ወይስ እሩቅ ነዉ ጩኸን እንጥራው ያ አሏህ ብለን? ብሎ ጠየቃቸው። ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) መልስ አልሰጡም። አሏህ ግን ለዚህ ሰው ለጠየቀው ጥያቄ መለስ ሰጠ። መልሱም እንዲህ ይላል፦ ወ ኢዛ ሰአለከ ዒባዲ ዓኒ(ባሮቼ ስለኔ ጉዳይ ከጠየቁህ) ፈኢኒ ቀሪብ(እኔ ቅርብ ነኝ) ኡጂቡ ዳዕወተ ዳዒ ኢዛ ደዓ (የተጣሪዎችን ጥሪ በጠሩኝ ግዜ እቀበላቸዋለው) በሚል የቁርኣን አያ አሏህ(ሱ.ወ) መልስ ሰጠ። ስለዚህ አሏህ ለእኛ ቅርብ ነው የትም እንሁን የት በምንም አይነት ችግርና በደል ላይ እንሁን ዱአችነን ወደ አሏህ ብቻ ነው ማድረግ ያለብን።
ሁለት የዱአ አይነቶች አሉ እነሱም፦
ዱአኡል መሰላህ ብሎ ማለት አሏህን የመለመን ዱአ ነው። ለምሳሌ አሏህ ሆይ ማረኝ ፣ አሏህ ሆይ መልካም ስራን ስጠኝ ፣ አሏህ ሆይ ልጅ ስጠኝ ፣ አሏህ ሆይ ባሪያህ አድርገኝ ወ.ዘ.ተ
ሁለተኛው የዱአ አአይነት ዱአኡል ኢባዳ ሲሆን ይህ የዱአ አይነት እያንዳንዱን የአምልኮተ አሏህ ተግባሮችን ያጠቃልላል። ለምሳሌ፦ ሶላት ፣ ዚክር ፣ ቲላወቲል ቁርአን ወ.ዘ.ተ
ትክክለኛና ሙሉ የሆነ ዱአ ማለት ሁለቱን የዱአ አይነቶችን ባንድ ላይ አጠቃሎ የያዘ ነው። አሏህን በብቸኝነት እየተገገዛን አሏህን ብቻ እንለምናለን (ሱረቱል ፍቲሃ :5)።
ዱአ ስናደርግ ምን ማድረግ አለብን?
በዱአ ውስጥ ማድረግ የተጠሉ ተግባራቶች አስር ናቸው። እነሱም፦ ግጥም ፣ ሃራም የሆነን ነገር መለመን ፣ አሏህ አስቀድሞ የደነገገውን ነገር መለመን ፣ ምድራዊ የሆኑ ነገሮችን ብቻ መለመን ፣ የአሏህን ስሞችና ባህሪያት ያላግባብ መጠቀም ፣ መጥፎ የሆነን ነገር ለራሳችነም ይሁን ለሌሎች መለመን ፣ ዱአ ያደረጉ መራገም ፣ ሞትን መለመን ፣ ይህን ስጠኝ እንጂ ሌላ አልጠይቅህም ማለት ፣ ጩኸው ዱአ ማድረግ ናቸው።
ዱአ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ጊዜዎች የሚከተሉት ናቸው። እነሱም፦ እኩለለሊት ፣ አዛን ሲደረግ ፣ በአዛንና በኢቃም መካከል ባለችው ጊዜ ፣ በሶላት ወቅት ፣ በሱጁድ ወቅት ፣ በጁምአ ቀን ፣ በረመዷን በተለይ በለይለቱል ቀድር ፣ ውዱእ ካደረጉ ቡኋላ ፣ የዘምዘም ውሃ ከመጠጣት በፊት ፣ በሐጅ ወቅት በተለይ በአረፋ ቀን ፣ ዝናብ ሲጥል
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|